From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
"በነገር ፡ ሁሉ ፡ በጸሎትና ፡ በምልጃ ፡ ከምሥጋና ፡ ጋር
በእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ልመናችሁን ፡ አስታውቁ ፡ እንጂ
በአንዳች ፡ አትጨነቁ"
ስለ ፡ እራሴ ፡ ስለ ፡ ግሌ
ስለ ፡ ቤቴ ፡ ስለ ፡ አገሬ
ስለ ፡ ኑሮ ፡ ስለ ፡ ሕይወት
ስለ ፡ ያዝኩት ፡ አገልግሎት
የማዋይህ ፡ አለኝና ፡ ልምበርከክ ፡ ፊትህ ፡ እንደገና
የማዋይህ ፡ አለኝና ፡ ልምበርከክ ፡ ፊትህ ፡ እንደገና (፪x)
የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያደስከው
ጓዴ/ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና
የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x)
"ያዕቆብ ፡ ግን ፡ ለብቻው ፡ ቀረ
አንድ ፡ ሰው ፡ እስኪነጋ ፡ ድረስ ፡ ይታገለው ፡ ነበር
እንዳላሸነፈውም ፡ ባየ ፡ ጊዜ ፡ የጭኑን ፡ ሽሉዳ??? ፡ ነካው
ያዕቆብም ፡ የጭኑን ፡ ??? ፡ ሲታገለው ፡ ደነዘዘ
እንዲህም ፡ አለው ፡ 'ሊነጋ ፡ አቅላልቷልና ፡ ልቀቀኝ'
እርሱም ፡ 'ካልባረከኝ ፡ አለቅህም' ፡ አለው
እንዲህም ፡ አለው ፡ 'ስምህ ፡ ማነው?'
እርሱም ፡ 'ያዕቆብ ፡ ነኝ ፡ አለው'
'ከእንግዲህ ፡ ወዲህ ፡ ስምህ ፡ እስራኤል
ይባላል ፡ እንጂ ፡ ያዕቆብ ፡ አይባልም'
በዚያም ፡ ስፍራ ፡ ባረከው።"
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ በቤቴ ፡ ላይ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ በአገሬ ፡ ላይ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ ቤተሰቤን ፡ ላይ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ ስራዬ ፡ ላይ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ ትምህርቴ ፡ ላይ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ ትዳሬ ፡ ላይ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
በረከትህን ፡ ልጥራ ፡ በእኔነቴ ፡ በዚህ ፡ ማለዳ
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፬x)
ካልዳሰስከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
ካልፈወስከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
ካለወጥከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
ካላደስከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)
|