የሰው ፡ ፍቅር (Yesew Feqer) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Lyrics.jpg


()

ሽሽ ፡ ወጣቱ ፡ ሽሽ
(Shesh Wetatu Shesh)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

አዝፍቅር (፯x) ፡ ፍቅር (፯x)
(የሰው ፡ ፍቅር) ዛሬ ፡ አብቦ ፡ ታይቶ
(የሰው ፡ ፍቅር) የማይጠፋ ፡ መስሎ
(የሰው ፡ ፍቅር) አብቦ ፡ ይረግፋል
(የሰው ፡ ፍቅር) ደምቆ ፡ እንደበራ ፡ በድንገት ፡ ይጠፋል

እኛ ፡ ግን ፡ እኛ ፡ ግን
ፍቅርን ፡ የምናውቀው
የዘለዓለሙን ፡ ነው (፪x)

አዝፍቅር (፯x) ፡ ፍቅር (፯x)
(የሰው ፡ ፍቅር) በቃል ፡ ድርዳሬ
(የሰው ፡ ፍቅር) አንደኛው ፡ በወሬ
(የሰው ፡ ፍቅር) ከቃላት ፡ አያልፍም
(የሰው ፡ ፍቅር) ተግባር ፡ ላይ ፡ ሲያመጡት ፡ በአጠገቡ ፡ አያልፍም

ለኛ ፡ ግን ፡ ለኛ ፡ ግን
ፍቅርን ፡ የምናውቀው
ተግባሩን ፡ አይተን ፡ ነው
ለኛ ፡ ግን ፡ እኛ ፡ ግን
ፍቅርን ፡ የምናውቀው
መስቀል ፡ ላይ ፡ ወጥቶ ፡ ነው (፪x)

አዝፍቅር (፯x) ፡ ፍቅር (፯x)
(የሰው ፡ ፍቅር) ከተነካ ፡ ጥቅሙ
(የሰው ፡ ፍቅር) ይጠፋል ፡ አቅሙ
(የሰው ፡ ፍቅር) የወደደ ፡ ይመስላል
(የሰው ፡ ፍቅር) ከመጥላት ፡ ከማጥፋት ፡ መቼ ፡ ይመለሳል

እኛ ፡ ግን ፡ እኛ ፡ ግን
ፍቅርን ፡ የምናምነው
ወዶ ፡ አድኖን ፡ ነው (፪x)

ፍቅር (፯x) ፡ ፍቅር (፯x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር