እጸልያለሁ (Etseleyalehu) - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት
(Getayawkal & Birucktawit)

Lyrics.jpg

()

የ፲፩ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ
(Ye11gnaw Seat Yetselot Teri)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(1)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal & Birucktawit)

ሊነጋጋ ፡ ሲል ፡ ኢየሱስ ፡ በማለዳ ፡ ተነስቶ ፡ ወጣ
ለመጸለይም ፡ ወደ ፡ አንድ ፡ ገለልተኛ ፡ ቦታ ፡ ሄደ

ሌሊቱ ፡ ሲነጋ ፡ ጐህ ፡ ሲቀድ
አእዋፍ ፡ ሲንጫጩ ፡ በአንድነት
በዜማ ፡ ፈጣሪን ፡ ለማምለክ
ሲወጡ ፡ ሁሉም ፡ ከያሉበት

እኔ ፡ ግን ፡ መኝታዬ ፡ ሞቀኝ
ዝምብለሽ ፡ ተኚ ፡ ተኚ ፡ ቢለኝ
መኝታዬን ፡ ወዲያ ፡ ገፍፌ
ለጸሎት ፡ ነቃሁኝ ፡ ከእንቅልፌ

ለጸሎት ፡ መንፈሴ ፡ ሲነቃ
ሥጋዬ ፡ ባይደሰት ፡ ቢከፋ
ሳይወድ ፡ በግዱ ፡ ያብርና
መጸለዬ ፡ ይቀጥላል ፡ ገና

ስሙን ፡ ስጠራው ፡ የጌታዬን
ያድሰዋል ፡ ደካማው ፡ ጐኔን
ቅባቱ ፡ መፍሰስ ፡ ይጀምራል
ለጸሎት ፡ ጉልበቴን ፡ ያድሳል

አዝእጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ መች ፡ አፍሬ ፡ አውቃለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ ድልን ፡ አግኝቻለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ መልስን ፡ አግኝቻለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ እንደሚሰማ ፡ አምናለሁ

አንዳንዴ ፡ ውስጤ ፡ ጸልይ ፡ ሲለኝ
ስጋዬ ፡ ግን ፡ ሲያታልለኝ
ቆይ ፡ ትጸልያለህ ፡ በኋላ
እያለ ፡ ጊዜዬን ፡ ሊበላ

ግን ፡ ዳንኤልን ፡ ጉድጓድ ፡ ያስጣለው
አትጸልይ ፡ የሚል ፡ ህግ ፡ ነው
ቢያስመርጡት ፡ ከምንም ፡ ነገር
ጸሎት ፡ ነው ፡ ለእርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነገር

ይህንን ፡ ሳስታውስ ፡ እነቃለሁ
ስጋዬን ፡ ተወኝ ፡ እለዋለሁ
ስታዘዝ ፡ ለነቃው ፡ መንፈሴ
ለጸሎት ፡ ተጋልኝ ፡ ጉልበቴ

ጸሎት ፡ ትልቅ ፡ መሳሪያዬ ፡ ነው
ሰይጣንም ፡ ይሄ ፡ ስለገባው
እንዳልጸልይ ፡ ቢታገለኝም
ምክኒያትን ፡ ለሥጋዬ ፡ አልሰጥም

አዝእጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ መች ፡ አፍሬ ፡ አውቃለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ ድልን ፡ አግኝቻለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ መልስን ፡ አግኝቻለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ እንደሚሰማ ፡ አምናለሁ

አንተ ፡ ግን ፡ ስትጸልይ ፡ ወደ ፡ እልፍኝህ ፡ ግባ
መዝጊያህንም ፡ ዘግተህ ፡ በስውር ፡ ላልው ፡ አባትህ ፡ ጸልይ
በስውር ፡ የሚያይ ፡ አባትህም ፡ በግልጥ ፡ ይከፍልሃል

ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ በሕይወቴ
መምበርከክ ፡ ሲያቅተው ፡ ጉልበቴ
ተስፋ ፡ በመቁረጥ ፡ ውስጥ ፡ ስሞላ
መፍትሄ ፡ መልስን ፡ ሳጣ ፡ መላ

ከመጸለይ ፡ ይልቅ ፡ በፊቱ
ሳወራ ፡ ላገኘሁት ፡ ሁሉ
ይባባስብኛል ፡ ችግሬ
ያጐብጠኛል ፡ ያ ፡ ጠብቆ ፡ ቀምበሬ

ግን ፡ በሬን ፡ ዘግቼ ፡ ስገባ
የውስጤን ፡ ሁሉ ፡ ወደ ፡ ሚረዳ
በጸሎት ፡ ዙፋኑ ፡ ስር ፡ ስወድቅ
ይታደሳል ፡ ውስጤ ፡ በድንገት

ያልወጣሁት ፡ ችግር ፡ ጸልዬ
ፍፁም ፡ የለምና ፡ በሕይወቴ
ባልጸልይ ፡ እራሴን ፡ እጐዳለሁ
ይህንን ፡ በተግባር ፡ አውቃለሁ

አዝእጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ መች ፡ አፍሬ ፡ አውቃለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ ድልን ፡ አግኝቻለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ መልስን ፡ አግኝቻለሁ
እጸልያለሁ (፫x) ፡ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ለምኜ ፡ እንደሚሰማ ፡ አምናለሁ