የተስፋው ፡ ቃል (Yetesfaw Qal) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 2008.jpg

፳ ፻ ፰
(2008)

ባርኮቴን ፡ ልቁጠረው
(Barkotien Lequterew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 8:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

ከዘመድ ፡ አዝማድህ ፡ ተለይተህ ፡ ውጣ
የሚልን ፡ ድምጽ ፡ ሰምቶ ፡ በእምነት ፡ የወጣ [1]
አብርሃም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መቶ ፡ ዕድሜ ፡ ሊሞላ
አስር ፡ አመት ፡ ቀረው ፡ ሊሻገር ፡ እርጅናን [2]
ሲዘገይ ፡ የተስፋው ፡ ቃልኪዳን ፡ ሲጠፋ
ከአብርሃምና ፡ ሳራ ፡ ተሟጠጠ ፡ ተስፋ
ሃሳባቸውን ፡ ሳቱ ፡ እስማኤልም ፡ መጣ [3]
ለዛ ፡ ጻድቅ ፡ ሰው ፡ ቤት ፡ ሁከትን ፡ አመጣ
ነገር ፡ ግን ፡ ለመቶ ፡ አንዲት ፡ አመት ፡ ስትቀር
የሳራን ፡ ማህጸን ፡ አሰበ ፡ እግዚአብሔር [4]
ይስሃቅ ፡ የተስፋው ፡ ልጅ ፡ ወዲያው ፡ ተወለደ
የተስፋው ፡ ጨለማ ፡ ተወገደ (፪x) [5]

አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም
መፈጸሙ ፡ አይቀርም
የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን
ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x)

እስራኤላውያን ፡ ከነዓን ፡ እንዳይገቡ
ጋሬጣ ፡ ሆነባቸው ፡ የእያሪኮ ፡ ግንቡ
ቀንደ ፡ መለከትን ፡ በእጃቸው ፡ ይዘው
በታላቅ ፡ ዝማሬ ፡ ሊነድሉት ፡ ቆርጠው
ፍፁም ፡ ሳይሰለቹ ፡ ህዝቡና ፡ እያሱ
የእያሪኮን ፡ ቅጥር ፡ ሊደረማምሱ
ቆርጠው ፡ ተነስተዋል ፡ ዙረት ፡ ጀምረዋል
ይኸው ፡ ሳይነደል ፡ ስድስት ፡ ቀን ፡ አልፎታል
ግን ፡ ለመጨረሻ ፡ መዞር ፡ ጀምረዋል
መለከት ፡ መንፋቱን ፡ ተያይዘውታል
በዚህ ፡ ታላቅ ፡ ተስፋ ፡ እያሪኮን ፡ ሲዞሩ
የእያሪኮን ፡ ቅጥር ፡ አፈረሱ (፪x)

አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም
መፈጸሙ ፡ አይቀርም
የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን
ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x)

ሃናም ፡ መካኗ ፡ ሴት ፡ ልጅን ፡ ያልወለደች
ለብዙ ፡ አመታት ፡ ብዙ ፡ ያለቀሰች
ሁልጊዜ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ፡ የምታፈስ ፡ እንባ
ከአስር ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ያልተሻላት ፡ ባሏ [6]
ወደ ፡ ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ስትጸልይ ፡ ገብታ
እንባዋን ፡ ስትዘራ ፡ ለላይኛው ፡ ጌታ
ካህኑ ፡ ኤሊ ፡ ግን ፡ ሰካራም ፡ ነሽ ፡ አላት
የልቧል ፡ ሰቆቃ ፡ መቼ ፡ ተረዳላት [7]
አምላኬ ፡ ልጅ ፡ ስጠኝ ፡ ለአንተው ፡ ሰጥሃለሁ
ይኸው ፡ ተንበርክኬ ፡ ቃልኪዳን ፡ እገባለሁ [8]
እያለች ፡ በተስፋ ፡ ስትጠብቅ ፡ ሳትሰለች
ሳሙኤልን ፡ . (1) . ፡ ወለደች (፪x) [9]

አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም
መፈጸሙ ፡ አይቀርም
የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን
ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x)

ማርያምና ፡ ማርታ ፡ ታላቅ ፡ ወንድማቸው
እጅግ ፡ የሚወዱትም ፡ ያ ፡ መመኪያቸው
አልዓዛር ፡ ታሞ ፡ አልጋ ፡ ላይ ፡ ተኝቷል
መሞቱም ፡ አይቀርም ፡ ብለውም ፡ ሰግተዋል
ቶሎ ፡ በአፋጣኝ ፡ መልዕክትን ፡ ሰደዱ
ወዳጁን ፡ ኢየሱስን ፡ ሊያስጠሩ ፡ ወደዱ
ግን ፡ የአላዓዛር ፡ ሀመም ፡ እያደረ ፡ ባሰ
እዛው ፡ በተኛበት ፡ ወንድማቸው ፡ ሞተ
ተስፋቸውን ፡ ቆረጡ ፡ ወስደውም ፡ ቀበሩት
አራት ፡ ቀን ፡ አለፈ ፡ ዋሻ ፡ ውስጥ ፡ ጣሉት
ግን ፡ በአራተኛው ፡ ቀን ፡ ያ ፡ ወዳጁ ፡ መጣ
ሟችሁን ፡ ከሙት ፡ በሃል ፡ አወጣ (፪x)

አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም
መፈጸሙ ፡ አይቀርም
የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን
ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x)

  1. ዘፍጥረት ፲፪ ፡ ፩ - ፮ (Genesis 12:1-6)
  2. ዘፍጥረት ፲፯ ፡ ፲፯ (Genesis 17:17)
  3. ዘፍጥረት ፲፮ ፡ ፩ - ፬ (Genesis 16:1-4)
  4. ዘፍጥረት ፲፯ ፡ ፲፯ - ፳፩ (Genesis 17:17-21)
  5. ዘፍጥረት ፳፩ ፡ ፪ - ፫ (Genesis 21:2-3)
  6. ፩ ሳሙኤል ፩ ፡ ፩ - ፰ (1 Samuel 1:1-8)
  7. ፩ ሳሙኤል ፩ ፡ ፲፪ - ፲፰ (1 Samuel 1:12-18)
  8. ፩ ሳሙኤል ፩ ፡ ፲ - ፲፩ (1 Samuel 1:10-11)
  9. ፩ ሳሙኤል ፩ ፡ ፳ (1 Samuel 1:20)