From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ልባምን ፡ ሴት ፡ ማን ፡ ሊያገኛት ፡ ይችላል
ከእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ካልሆነ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
ከዝርግፍ ፡ ጌጥ ፡ ይልቅ ፡ ውስጧ ፡ የበለጠ
በፀጋው ፡ መንፈሷ ፡ ሁሉ ፡ ያጌጠ
ወርቅ ፡ አያምራት ፡ እርሷ ፡ ራሷ ፡ ወርቅ ፡ ናት
ለይሉኝታ ፡ ምታስመጣው ፡ ጥሎሽ ፡ የላት
መልካም ፡ አእምሮ ፡ የበሰለ ፡ ባህሪ
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ፈሪ
አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
ከውጭ ፡ ውበት ፡ የውስጥ ፡ ውበቷ ፡ በልጧል
አካሄዷ ፡ ንግግሯ ፡ ይገልጣል
ማስተዋሏ ፡ ዕውቀቷ ፡ የበዛ ፡ ነው
የማመዛዘን ፡ ችሎታ ፡ ሁሉ ፡ ያለው (በጣም)
እንደ ፡ ሰነፍ ፡ ሴቶች ፡ አትናገርም
በመከራም ፡ ውስጥ ፡ ተስፋን ፡ አትቆርጥም
ከአጥንቱ ፡ ነው ፡ እርሷ ፡ የተሰራችው
ለዚህ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ የቻለችው
አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
የባሏም ፡ ልብ ፡ ይተማመንባታል
እውነተኛው ፡ ፍቅር ፡ ይመግባታል
ትገዛለች ፡ ለቃሉ ፡ ለሃሳቡ
በግድ ፡ ሳይሆን ፡ አሸንፏት ፡ ፍቅሩ
ተወስና ፡ እርሷ ፡ ለእርሱ ፡ ተሰጥታ
በሌላ ፡ ወንድ ፡ ልቧም ፡ ሳያመነታ
አንድ ፡ ለአንድ ፡ አይደለም ፡ የእርሷ ፡ ሂሳብ
እንደቃሉ ፡ አንድ ፡ ናት ፡ ያለ ፡ ሃሳብ
አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
ገና ፡ ሌሊት ፡ በማለዳ ፡ ተነስታ (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት)
ምግብ ፡ ለቤቷ ፡ ሰዎች ፡ ሁሉ ፡ ሰርታ (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት)
ወገቧን ፡ በመቀነቷ ፡ ታጥቃለች (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት)
ስራዋን ፡ በጊዜው ፡ ትጨርሳለች (እንዲህ ፡ አይነቷ)
እንድትለፋ ፡ አይደለም ፡ እርሱ ፡ ያገባት (እንዲህ ፡ አይነቷ)
እረዳት ፡ ናት ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ የገባት (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት)
ሰራተኛው ፡ አይደለችም ፡ ለቤቱ (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት)
ናት ፡ ለባሏ ፡ ድምቀቱ ፡ ውበቱ (እንዲህ ፡ አይነቷ)
አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
ውበት ፡ ሃሰት ፡ ነው ፡ ደምግባትም (ከንቱ ፡ ነው)
ውበት ፡ ሃሰት ፡ ነው ፡ ደምግባትም (ከንቱ)
እግዚአብሔርን ፡ የምትፈራ ፡ ሴት ፡ እርሷ ፡ ትመሰገናለች (ትመሰገናለች)
እግዚአብሔርን ፡ የምትፈራ ፡ ሴት ፡ እርሷ ፡ ትመሰገናለች (እርሷ) (፪x)
እግዚአብሔርን ፡ የምትፈራ ፡ ሴት ፡ እርሷ ፡ ትመሰገናለች (፪x)
አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፬x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፬x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፬x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
|