የትዳር ፡ ዘለቄታ (Yetedar Zeleqieta)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ውበት ፡ ሐሰት ፡ ነው ፡ ሃላፊ
ደም ፡ ግባትም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ጠፊ
በሥጋ ፡ ላይ ፡ ጐጆ ፡ ተቀልሶ
መፍረሱ ፡ አይቀርም ፡ ተመልሶ

አዝ፦ የትዳር ፡ ዘለቄታ ፡ ልማቱ
አምላክ ፡ ሲሆን ፡ ነው ፡ መሠረቱ (፪X)

ቢትረፈረፍ ፡ ምድራዊ ፡ ንብረት
ምንም ፡ ቢደላን ፡ በዝቶ ፡ ምቾት
ሞልቶ ፡ ቢተርፍም ፡ ብር ፡ ወርቁ
ለብቻቸው ፡ ኑሮን ፡ አያደምቁ

አዝ፦ የትዳር ፡ ዘለቄታ ፡ ልማቱ
አምላክ ፡ ሲሆን ፡ ነው ፡ መሠረቱ (፪X)

ጌታ ፡ ራሱ ፡ ቤትን ፡ ካልሠራ
ጋብቻን ፡ ባርኮ ፡ ካልመራ
ሰዎች ፡ ቢሹ ፡ ጉድለት ፡ ሊያሟሉ
አይሳካም ፡ እንዲያው ፡ ይደክማሉ

አዝ፦ የትዳር ፡ ዘለቄታ ፡ ልማቱ
አምላክ ፡ ሲሆን ፡ ነው ፡ መሠረቱ (፪X)