የጥንት ፡ ታሪክ ፡ ንገረኝ (Yetent Tarik Negeregn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የጥንት ፡ ታሪክ ፡ ንገረኝ ፡ ስለ ፡ አዲሷ ፡ አገር
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅርና ፡ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር
እንዲገባኝ ፡ አድርገህ ፡ ታሪኩን ፡ ንገረኝ
ኃጢአት ፡ ያረከሰኝ ፡ ነኝ ፡ ፍቅሩም ፡ የማይገባኝ

አዝ፦ እኔም ፡ እንዳይጠፋኝ ፡ ያንን ፡ ስሙን ፡ እንዳከብር
ያንን ፡ ታሪክ ፡ ንገረኝ (፫x)
በመስቀሉ ፡ ይቅር ፡ አለኝ (፪x)
እዳዬን ፡ ከፈለልኝ

በቀስታ ፡ ንገረኝ ፡ በደንብ ፡ እንዲገባኝ
አስደናቂውን ፡ መዳን ፡ አምላክ ፡ የሰጠኝን
ብዙ ፡ ጊዜም ፡ ንገረኝ
የማለዳ ፡ ጤዛ ፡ ፈጥኖ ፡ እንደሚጠፋ

አዝ፦ እኔም ፡ እንዳይጠፋኝ ፡ ያንን ፡ ስሙን ፡ እንዳከብር
ያንን ፡ ታሪክ ፡ ንገረኝ (፫x)
በመስቀሉ ፡ ይቅር ፡ አለኝ (፪x)
እዳዬን ፡ ከፈለልኝ

አለስልሰህ ፡ ንገረኝ ፡ ድምጽህን ፡ አጣፍጠህ
ኢየሱስ ፡ እኔን ፡ ሊያድን ፡ እንደመጣ ፡ አውቀህ
ደጋግምና ፡ ንገረኝ ፡ የኢየሱስን ፡ ታሪክ
ደሙን ፡ ስላፈሰሰ

አዝ፦ እኔም ፡ እንዳይጠፋኝ ፡ ያንን ፡ ስሙን ፡ እንዳከብር
ያንን ፡ ታሪክ ፡ ንገረኝ (፫x)
በመስቀሉ ፡ ይቅር ፡ አለኝ (፪x)
እዳዬን ፡ ከፈለልኝ