ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ ፡ ነገንም (Zarien Yasaderegn Amnalehu Negenim)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከእሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያወጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሐሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ ፡ ነገንም ፡ ሊታደገኝ ፡ (፪X)

ማሰቤና ፡ መጨነቄ
የነገንም ፡ ምኑን ፡ አውቄ
የዛሬን ፡ ሸክም ፡ ያገዘኝ
አምናለሁ ፡ ነገን ፡ ሊታደገኝ

ከእሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያወጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሐሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ ፡ ነገንም ፡ ሊታደገኝ ፡ (፪X)

በዕምነት ፡ መኖር ፡ ተምሬአለሁ
ዓይኔን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ
ካላሳቤ ፡ ሆኖልኛል
ዘወትር ፡ ኢየሱስ ፡ ያግዘኛል

ከእሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያወጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሐሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ ፡ ነገንም ፡ ሊታደገኝ ፡ (፪X)

ከኃጢአት ፡ ከተማ ፡ የጠራኝ
ለምድርም ፡ ኑሮ ፡ የማይተወኝ
ውርደት ፡ ቀምሶአል ፡ ፍቅር ፡ ብሎ
ይጠራኛል ፡ ጌታ ፡ አክብሮ

ከእሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያወጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሐሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ ፡ ነገንም ፡ ሊታደገኝ ፡ (፪X)