From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
። ዓይኖቼ ወዳንተ ሲቀኑ፥ ወዳንተ ሲቀኑ፥ ወዳንተ ሲቀኑ፣
። ኢየሱስ ቀናልኝ መንገዴ ብሩ ሆነ ቀኑ፤ ብሩህ ሆነ ቀኑ።
አንድ ችግር በመንገዴ እኔን ሲገጥመኝ፣
እዚያና እዚያ ስቅበዘበዝ መፍትሔ ላገኝ፣
ትዝ ትለኝና አንተን አስባለሁ፣
አይኖቼን ወዳንተ አቀናለሁ፤
ከችግሬም ቶሎ እፈታለሁ።
። ዓይኖቼ ወዳንተ ...
እመካብሀለሁ ጌታ ሁሉን ቻይ ነህ፣
የሚያስፈራራኝን ሁሉ ትሽራለህ፤
የጠላት ቀስቱንም ሰብረህ አይቻለሁ፣
ኤልሻዳይ አምላኬ እታመንሃለሁ፤
ዘላለም በቤትህ መኖር መርጫለሁ።
|