የኢየሱስ ፡ ድምፅ (Yeyesus Demts)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የኢየሱስ ፡ ድምፅ ፡ ሲለኝ ፡ ሰማሁ
"ና ፡ ወደ ፡ ዕረፍቴ"
"አንተ ፡ የደከመህ ፡ ሰው ፡ ሆይ  !"
"እረፍ ፡ በብብቴ"
ወደርሱ ፡ መጣሁ ፡ በድካም
በሃዘንም ፡ ሳለሁ
እርሱ ፡ ደስታን ፡ ስለሰጠኝ
ዕረፍትን ፡ አገኘሁ

የኢየሱስ ፡ ድምፅ ፡ ሲለኝ ፡ ሰማሁ
"እነሆ ፡ ሰጠሁህ"
"የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ ጠጣ"
"አንተ ፡ የተጠማህ ፡ ሰው  !"
ወደርሱ ፡ መጣሁ
ሕይወትን ፡ ከሚሰጠው ፡ ጠጣሁ
ነፍሴ ፡ ከሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ረካች
በእርሱም ፡ እኖራለሁ

የኢየሱስ ፡ ድምፅ ፡ ሲለኝ ፡ ሰማሁ
"የዓለም ፡ ብርሃን ፡ ነኝ"
"ብርሃንህ ፡ ይወጣልሃል"
"እኔን ፡ ተመልከተኝ"
ወደርሱም ፡ አየሁ
ፀሐዬን ፡ ኮከቤን ፡ አገኘሁ
ጉዞዬ ፡ እስኪፈጸም ፡ አብረን ፡ እንሄዳለን