ዝናህ ፡ የገነነው ፡ በዓለም ፡ ላይ (Zenah Yegenenew Bealem Lay)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ልጽና ፡ በመንፈስህ ፡ እንዳልረታ
አርቄ ፡ እያየሁ ፡ ጽድቅ ፡ አክሊሌን
በተስፋ ፡ እንድጓዝ ፡ እርዳኝ ፡ ልጅህን
የርስቴ ፡ መያዣ ፡ መንፈስህ
ያጽናናኝ ፡ ሁልጊዜ ፡ እንዳልረሳህ
የማትሰለቸኝ ፡ የማትረሳኝ
ረዳት ፡ ለጉዞዬ ፡ ለነፍሴ ፡ አጽናኝ
ዓይኔን ፡ እንዳላነሳው ፡ ከመስቀልህ
ሃሣቤን ፡ ጠቅልለው ፡ ወደ ፡ ሞትህ
ዓይኔን ፡ እንዳላነሳው ፡ ከመስቀልህ
ሃሣቤን ፡ ጠቅልለው ፡ ወደ ፡ ሞትህ
ዝናህ ፡ የገነነው ፡ በዓለም ፡ ላይ
መቼ ፡ ትመጣለህ ፡ ፊትህን ፡ እንዳይ?
በጣም ፡ ጓጉቻለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ኢየሱሴ ፡ እንዳይህ ፡ ማራናታ!
በጣም ፡ ጓጉቻለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ኢየሱሴ ፡ እንዳይህ ፡ ማራናታ!
|