ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ ፡ ነገም (Zarien Yasaderegn Amnalehu Negem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ከሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያውጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሃሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ
ነገንም ፡ ሊታደገኝ (፪x)

ማሰቤና ፡ መጨነቄ
የነገንም ፡ ምኑን ፡ አውቄ
የዛሬን ፡ ሸክም ፡ ያገዘኝ
አምናለሁ ፡ ነገን ፡ ሊታደገኝ

አዝ፦ ከሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያውጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሃሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ
ነገንም ፡ ሊታደገኝ (፪x)

በእምነት ፡ መኖር ፡ ተምሬያለሁ
ዓይኔን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ
ካለ ፡ ሃሳቤ ፡ ሆኖልኛል
ዘወትር ፡ ኢየሱስ ፡ ያግዘኛል

አዝ፦ ከሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያውጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሃሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ
ነገንም ፡ ሊታደገኝ (፪x)

ከኃጢአት ፡ ከተማ ፡ የጠራኝ
ለምድርም ፡ ኑሮ ፡ የማይተወኝ
ውርደት ፡ ቀምሶአል ፡ ፍቅር ፡ ብሎ
ይጠራኛል ፡ ጌታ ፡ አክብሮ

አዝ፦ ከሾሃማው ፡ ሃገር ፡ ከቆንጥሩ
ያውጣኝ ፡ ያውቃል ፡ ከሃሩሩ
ዛሬን ፡ ያሳደረኝ ፡ አምናለሁ
ነገንም ፡ ሊታደገኝ (፪x)