የፀሎት ፡ ሰዓት (Yetselot Seat)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የፀሎት ፡ ሰዓት ፡ የደስታ ፡ ሰዓት ፡
ከዓለም ፡ የምሸሽበት ፡ አባቴንም ፡ የምሻበት
ምኞቴን ፡ የምነግርበት ፡
ከመከራ ፡ እርቃለሁ ፡ ጽናቴንም ፡ አገኛለሁ
ከፈተናም ፡ እድናለሁ ፡ ለፀሎትም ፡ እቀርባለሁ

የፀሎት ፡ ሰዓት ፡ የደስታ ፡ ሰዓት
ፀሎቴም ፡ የሚሰማበት
አምላኬን ፡ የማገኝበት
ነፍሴ ፡ የምትረካበት
ወደ ፡ ዙፋኑም ፡ ከጠራኝ
ፀጋዬን ፡ ታመን ፡ ካለኝ
ችግሬንም ፡ እጥላለሁ
እርሱንም ፡ እለምናለሁ

የፀሎት ፡ ሰዓት ፡ የምወደው
መጽናናቱን ፡ ልካፈለው
የሰማይን ፡ ቤት ፡ እስካየው
ሩጫዬን ፡ እስክጨርሰው
በማይሞት ፡ ሥጋ ፡ እነሣለሁ
ዋጋዬንም ፡ እወስዳለሁ
በእልልታም ፡ እውላለሁ
ሳመሰግን ፡ እኖራለሁ