የተሰቀለውን ፡ መድኅን ፡ ለነፍስህ ፡ ብታይ (Yeteseqelewun Medhin Lenefsih Btai)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የተሰቀለውን ፡ መድኅን ፡ ለነፍስህ ፡ ብታይ
ይሆንልሃል ፡ ምሉዕ ፡ መዳን
ና! ተመልከት ፡ ሲሳቀይ ፡ በመስቀሉ ፡ ላይ
ሲሽርም ፡ የሞትን ፡ ሥልጣን
እይ ፣ እይና ፡ ዳን
የተሰቀለውን ፡ መድኅን ፡ በዕምነት ፡ ብታይ
ይሆንልሃል ፡ ምሉዕ ፡ መዳን

ብትጦም ፡ ብትፀልይም ፡ ዕንባህ ፡ ሲፈስ
ያ ፡ አይበቃም ፡ ለነፍስህ ፡ መዳን
የመድኃኒቱ ፡ ደም ፡ ግን ፡ በመስቀል ፡ ሲፈስ
ተፈጸመ ፡ የእኛ ፡ መዳን
እይ ፣ እይና ፡ ዳን
የተሰቀለውን ፡ መድኅን ፡ በዕምነት ፡ ብታይ
ይሆንልሃል ፡ ምሉዕ ፡ መዳን

ኃጢአትህ ፡ በላይህ ፡ የቀረ ፡ ቢሆን
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ለምን ፡ ተቀሠፈ?
የተቀደሰ ፡ ደሙም ፡ ባይከፍል ፡ ዕዳህን
ከጐኑስ ፡ ለምን ፡ ጐረፈ?
እይ ፣ እይና ፡ ዳን
የተሰቀለውን ፡ መድኅን ፡ በዕምነት ፡ ብታይ
ይሆንልሃል ፡ ምሉዕ ፡ መዳን

ትሩፋቱን ፡ ተቀበል ፡ በስሙም ፡ ዕመን
የመድኃኒቱን ፡ ደም ፡ አትናቅ
በተሠዋ ፡ ጊዜ ፡ በተሰቀለም ፡ ቀን
ከሞት ፡ እንዳዳነህ ፡ ዕወቅ
እይ ፣ እይና ፡ ዳን
የተሰቀለውን ፡ መድኅን ፡ በዕምነት ፡ ብታይ
ይሆንልሃል ፡ ምሉዕ ፡ መዳን