የተመረጡ ፡ በሰማያት (Yetemerettu Besemayat)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የተመረጡ ፡ በሰማያት
የሚያገኟት ፡ ብፅዕናን
ሰው ፡ በሕልሙም ፡ ቢሆን ፡ አላያት
አይተርካትም ፡ የሰው ፡ ልሣን
ግሩም ፡ የሆነ ፡ የትንግርት ፡ ነገር
በአዲሱ ፡ ኢየሩሣሌም
እየታየን ፡ የአምላክ ፡ ፍቅር
እንቀምሳለን ፡ ለዘለዓለም ።

ዲዳ ፡ ድኖ ፡ ሲያመሰግን
ሽባም ፡ በደስታ ፡ ይዘልላል
ምኞት ፡ የለንም ፡ በልባችን
የምንመኘው ፡ ይፈጸማል
የዓለም ፡ መከራ ፡ ከኛ ፡ ጠፍቶ
ፍፁም ፡ ሰላም ፡ ይሆነናል
በመቃብርም ፡ ደዌ ፡ ቀርቶ
ጤና ፣ ብፅዕናም ፡ ይሰጠናል ።

ጣፋጩ ፡ ሰማያዊ ፡ መና
ዘለዓለማዊ ፡ ምግባችን ፡ ነው
ንጉሡንም ፡ በታላቅ ፡ ግርማ
በዓይናችን ፡ ልንመለከተው
ጉድለት ፡ የለም ፡ በዕውቀታችን
ፍቅርም ፡ አይቀዘቅዝም
ልውጥ ፡ ነው ፡ ምስኪኑ ፡ ሥጋችን
ከንግዲህ ፡ ወዲያም ፡ አይሞትም ።

የተወደደችው ፡ ሙሽራ
ድና ፡ ታያለች ፡ ሙሽራዋን
ትኖራለች ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
ስታመሰግን ፡ አምላኳን
ኦ! መድኃኒቴ ፡ ያን ፡ ብፅዕና
ስለ ፡ ቸርነትህ ፡ ስጠኝ
እኔን ፡ ደግሞ ፡ የአንተን ፡ ምሥጋና
ወደሚዘምሩት ፡ አድርሰኝ ።