የኢየሱስን ፡ ሥም ፡ ተቀበል (Yeyesusen Sem Teqebel)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የኢየሱስን ፡ ሥም ፡ ተቀበል
አንተ ፡ ችግረኛ ፡ ልጅ
መጽናናትን ፡ እንዲሰጥህ
በምትሄድበት ፡ ሁሉ

አዝ፦ ክቡር ፡ ሥም ፡ ጣፋጭ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ ነው (፪x)

የእርሱን ፡ ሥም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ወስደህ
እንደ ፡ ጋሻህ ፡ አድርገው
ፈተና ፡ ቢመጣብህም
በፀሎት ፡ ወደርሱ ፡ ሂድ

አዝ፦ ክቡር ፡ ሥም ፡ ጣፋጭ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ ነው (፪x)

የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ የከበረው
ልባችንን ፡ ያስደስታል
በፍቅሩ ፡ ይቀበለናል
ስናወድሰው ፡ ስንኖር

አዝ፦ ክቡር ፡ ሥም ፡ ጣፋጭ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ ነው (፪x)

በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ እንበርከክ
ከዙፋኑ ፡ ፊት ፡ ቀርበን
የገዦችን ፡ ገዥ ፡ እናንግሥ
ጉዟችንን ፡ ስንጨርስ

አዝ፦ ክቡር ፡ ሥም ፡ ጣፋጭ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ ነው (፪x)