እንዳንተ ያለ የለምና (እንዳንተ ያለ የለምና)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፡ እንዳንተ ያለ የለምና በቃሉ የጸና
ኪዳንህን ጠባቂ ነህ እንደ አፍህ ትሆናለህ
ለስምህ ይሁን ምስጋና
እንዳንተ ያለ የለምና

ልበ ሰፊ ታጋሽ አባት
ቋሚ ወዳጅ በላይ ከናት
እንዳንተ ያለ አላየንም
በጆሮአችን አልሰማንም

ለተጠማ የሕይወት ውሃ
ለቆዘመ ነህ ፍሥሀ
የዘላለም ሰላም ደስታ
የተሰዋህ በጎልጎታ

ጠባቂ አለን የማይተኛ
ቀን ከሌሊት ጋሻ ለኛ
ጨካኝ አይደል ወይ ምንደኛ
ጌታ ኢየሱስ እውነተኛ

This song was sang by Ethiopian EVangelical Church in Nairobi Choir.