የጥንት ፡ አምባ ፡ ጥግ ፡ ሁነኝ (Yettint Amba Ttig Hunegne)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
የጥንት ፡ አምባ ፡ ጥግ ፡ ሁነኝ
ከለላህ ፡ ይሠውረኝ
ከተወጋው ፡ ጐድንህም
የሚፈልቅ ፡ ውሃና ፡ ደም
ከክፋቴ ፡ ያጥራኝ
ከጥፋትም ፡ ያድነኝ
ሕግህን ፡ መፈጸሙ
አቅቶኝ ፡ ተሸነፍሁ
ሌትም ፡ ቀንም ፡ አልቅሼ
አልጠራልኝም ፡ ዕድፌ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ተስፋዬ
ያድነኝ ፡ ከኩነኔ
የምሰጥህ ፡ የለኝም
ፅድቅ ፡ አልተገኘብኝም
አንተ ፡ ብቻ ፡ ፅድቅ ፡ ሁነኝ
ፀጋህ ፡ ብቻ ፡ ያድነኝ
ቅዱስ ፡ ደምህ ፡ አምላኬ
ይሁንልኝ ፡ ሕይወቴ
የፍርድ ፡ ዕለትም ፡ ሲደርስ
ምድራችንም ፡ ሲፈርስ
ዓለም ፡ ካይንህ ፡ ፊት ፡ ሲቀልጥ
ፅድቅህንም ፡ ስትገልጥ
የጥንት ፡ አምባ ፡ ጥግ ፡ ሁነኝ
ከለላህ ፡ ይሠውረኝ
|