የጽዮን ፡ ግንብ ፡ ጠባቂ ፡ ሆይ (Yetsion Genb Tebaqi Hoy)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የጽዮን ፡ ግንብ ፡ ጠባቂ ፡ ሆይ
ስለ ፡ ሌቱ ፡ ንገረን
ቀኑ ፡ ሊነጋ ፡ ብሏልን ፡ ንጋቱስ ፡ ሊወጣልን
አብራልነ ፡ አሁን ፡ የብርሃን ፡ ጮራ (፪x)

ወሰኑን ፡ አልፈነዋል ፡ ወይ ፡ ጌታ ፡ እስኪ ፡ ንገረን
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ቀርበናል ፡ ወይ
አገሩስ ፡ ይታያል ፡ ወይ
የሰማዩ ፡ መንግሥትህ ፡ ቀርቧል ፡ ወይ (፪x)

ብርሃን ፡ በርቷል ፡ ቀንም ፡ መጥቷል
አንድ ፡ ላይ ፡ ዕልል ፡ እንበል
የአጥቢያ ፡ ኮከብ ፡ ተነሣልን ፡ በሰማይ ፡ የሚያበራ
ቅዱሣን ፡ ሁሉ ፡ በጣም ፡ ተደሰቱ (፪X)

የሰማይ ፡ መሪ ፡ ተገኝቷል
መድረሳችን ፡ እርግጥ ፡ ነው
ቶሎ ፡ ቶሉ ፡ እንራመድ ፡ ከግባችን ፡ ለመድረስ
ድምጻችንን ፡ እናንሳ ፡ በደስታ (፪X)