From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
የተባረከ ፡ ሰዓት ፡ ነው ፡ የምንጸልይበት
ወደ ፡ አምላካችን ፡ ኢየሱስ ፡ የምንቀርብበት
በሃይማኖት ፡ ብንቀርበው ፡ እርሱ ፡ ያስጠጋናል
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
አዝ፦ የጸሎት ፡ ጊዜ ፡ የተባረከ
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው ?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
የተባረከ ፡ ሰዓት ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የሚቀርበን
በርህራሄ ፡ ፍቅር ፡ ልጆቹን ፡ ሊሰማ
ሸክማችንን ፡ ከጫማው ፡ እንድንጥል ፡ ሲነግረን
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
አዝ፦ የጸሎት ፡ ጊዜ ፡ የተባረከ
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው ?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
የተባረከ ፡ ሰዓት ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ለቆረጡ
ለኢየሱስ ፡ ችግራቸውን ፡ ያቀርባሉ
በርህሩህ ፡ ልቡ ፡ ኢየሱስ ፡ ያሳርፋቸዋል
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
አዝ፦ የጸሎት ፡ ጊዜ ፡ የተባረከ
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው ?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
የተባረከ ፡ ሰዓት ፡ ነው ፡ በጌታ ፡ ስናምን
እርሱ ፡ ይሰጠናል ፡ የምንፈልገውን
ሥቃይ ፡ ችግርም ፡ ያልፋል ፡ በእርሱ ፡ ኃይል ፡ ስናምን
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
አዝ፦ የጸሎት ፡ ጊዜ ፡ የተባረከ
እንዴት ፡ ጣፋጭ ፡ ዕረፍት ፡ ነው ?
በዚያ ፡ መሆን ፡ ውብ ፡ ነው
|