ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስለእኛ ፡ መከራ ፡ ተቀበለ (Eyesus Kristos Silegna Mekera Teqebele)
From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስለእኛ
መከራ ፡ ተቀበለ
እርሱም ፡ እንደ ፡ በደለኛ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ ተሰቀለ
ቤዛ ፡ እርሱ ፡ ሆኗል
በኛም ፡ ፈንታ ፡ ሞቷል
በሕማማቱ ፡ በሞቱም
ምሕረት ፡ ተዋጅቶልናል
በትንሣዔውም ፡ በሕይወቱም
ጽድቅም ፡ ተገኝቶልናል
በዕርገቱም ፡ ወደ ፡ ላይ
ሥፍራ ፡ ሰጠን ፡ በሰማይ
ምሥጉን ፡ እርሱን ፡ የሚያምን
የሚቀበል ፡ ፀጋውን
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ አለው
ችጋረኛ ፡ ቢሆንም
ከምድር ፡ ወደ ፡ ሕይወት
ይገባል ፡ በሃይማኖት
|