የምሥራችን ፡ ሰምተህ ፡ እመን (Yemsirachn Semteh Emen)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የምሥራችን ፡ ሰምተህ ፡ እመን
ኢየሱስ ፡ ፈጽሞ ፡ አዳነን
ሰውን ፡ ሊያድን ፡ በምሕረት ፡ ነው
የጥንቱ ፡ የዓብ ፡ ሥምረት
ወልድም ፡ ዋጀልን ፡ ሥርየት

የምሥራችን ፡ ሰምተህ ፡ እመን
ኢየሱስ ፡ ፈጽሞ ፡ አዳነን
ብቻውን ፡ ሆኖ ፡ ድል ፡ ነሥቷል
የእባብን ፡ ራስ ፡ ረግጧል
ሰማይን ፡ ከፍቶልናል

የምሥራችን ፡ ሰምተህ ፡ እመን
ኢየሱስ ፡ ፈጽሞ ፡ አዳነን
ሕግ ፡ ሊሠራ ፡ የማይችለውን
በአንተም ፡ ውስጥ ፡ የሚነቅፈውን
ኢየሱስ ፡ ተሸክሞታል

የምሥራችን ፡ ሰምተህ ፡ እመን
ኢየሱስ ፡ ፈጽሞ ፡ አዳነን
ኃጢአትህ ፡ ከብዶብሃል
መርገምም ፡ ተጭኖብሃል
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ አድኖሃል

የምሥራችን ፡ ሰምተህ ፡ እመን
ኢየሱስ ፡ ፈጽሞ ፡ አዳነን
ርኩስ ፡ ኃጢአተኛ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ስለወደደህ
ከአምላክ ፡ ጋር ፡ አስታረቀህ

ተቀብለህ ፡ ደስ ፡ ይበልህ
ኢየሱስ ፡ ሁሉ ፡ ሲሆንልህ
ሁሉን ፡ የሚያስፈልገው
በመድኃኒቱ ፡ ያገኘው
ጻድቅም ፡ ቅዱሥም ፡ ነው

ተቀብለህ ፡ ደስ ፡ ይበልህ
ኢየሱስ ፡ ሁሉ ፡ ሲሆንልህ
ስትጨነቅ ፡ ይጦርሃል
ባይታይልህም ፡ ቀርቦልሃል
በእጁም ፡ ይሸከምሃል

ተቀብለህ ፡ ደስ ፡ ይበልህ
ኢየሱስ ፡ ሁሉ ፡ ሲሆንልህ
እንግድነትና ፡ ድካም
አርቆልህ ፡ ያሳርፍሃል
በሰማያዊ ፡ ሰላም