From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
እጅግ ፡ በረዘመው ፡ የኢያሪኮ ፡ ቅጥር
ነፍሴ ፡ ብትጨነቅ ፡ ለሞት ፡ ብታጣጥር
አልጠፋም ፡ ከልቤ ፡ ያለፈው ፡ ትዝታ
ዛሬም ፡ ድል ፡ የአንተነው ፡ ነው ፡ ቅዱስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አዝ፦ የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ተራራውን ፡ ንደህ ፡ ባሕሩን ፡ ትከፍላለህ
ዮርዳንስም ፡ ቆሞ ፡ በድል ፡ አልፌአለሁ
በኢያሪኮም ፡ ላይ ፡ ክንድህን ፡ አያለሁ
የቃል ፡ ኪዳን ፡ ታቦት ፡ ከፊቴ ፡ መቅደሙ
ምልክት ፡ ይሆናል ፡ ጠላት ፡ ለመውደሙ
እኔም ፡ እነፋለሁ ፡ ቀንደ ፡ መለከቴን
ዓለም ፡ ሁሉ ፡ ያያል ፡ አሸናፊነቴን
አዝ፦ የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ተራራውን ፡ ንደህ ፡ ባሕሩን ፡ ትከፍላለህ
ዮርዳንስም ፡ ቆሞ ፡ በድል ፡ አልፌአለሁ
በኢያሪኮም ፡ ላይ ፡ ክንድህን ፡ አያለሁ
ዮርዳኖስ ፡ ሲከፈል ፡ በድል ፡ ስንሻገር
አሸናፊነትን ፡ ለዓለም ፡ ልናገር
ከላይ ፡ ያስቀመጥነው ፡ መታሰቢያ ፡ ድንጋይ
ምስክራችን ፡ ነው ፡ ጠላታችን ፡ እንዲያይ
አዝ፦ የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ተራራውን ፡ ንደህ ፡ ባሕሩን ፡ ትከፍላለህ
ዮርዳንስም ፡ ቆሞ ፡ በድል ፡ አልፌአለሁ
በኢያሪኮም ፡ ላይ ፡ ክንድህን ፡ አያለሁ
የኢያሪኮ ፡ ቅጥር ፡ በእምነት ፡ ይፈርሳል
ብሩ ፡ ወርቁ ፡ ሁሉ ፡ ለምርኮ ፡ ይሆናል
የጠላትን ፡ ሰፈር ፡ በእሳት ፡ አጋያለሁ
አንተም ፡ ስትከብር ፡ በገሃድ ፡ አያለሁ
አዝ፦ የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ተራራውን ፡ ንደህ ፡ ባሕሩን ፡ ትከፍላለህ
ዮርዳንስም ፡ ቆሞ ፡ በድል ፡ አልፌአለሁ
በኢያሪኮም ፡ ላይ ፡ ክንድህን ፡ አያለሁ
|