የሚመጣ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ይላል (Yemimeta Hulu Eyesus Yilal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የሚመጣ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ይላል
ሰምቶ ፡ የሚመጣውንም ፡ ይቀበላል
አንድም ፡ ወደ ፡ ሜዳ ፡ ከቶ ፡ እንዳይጣል
ቃሉ ፡ ይመሰክራል
ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ ሲል ፡ ይጠራናል
ድምጹ ፡ ለሁላችንም ፡ ይሰማናል
ለጠፋው ፡ ልጅ ፡ አባቱ ፡ ተመለስ ፡ ይለዋል
እኛንም ፡ ይጠብቃል

ዕውነተኛ ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኗል
የሰማይም ፡ ደጅ ፡ በእርሱ ፡ ተከፍቷል
አንተም ፡ ለመግባት ፡ አሁን ፡ ይቻልሃል
ለአንተም ፡ ተከፍቶልሃል
ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ ሲል ፡ ይጠራናል
ድምጹ ፡ ለሁላችንም ፡ ይሰማናል
ለጠፋው ፡ ልጅ ፡ አባቱ ፡ ተመለስ ፡ ይለዋል
እኛንም ፡ ይጠብቃል

የሚመጣ ፡ ሁሉ ፡ ፀጋ ፡ ያገኛል
የኢየሱስን ፡ ትሩፋት ፡ ይቀበላል
ከሞት ፡ ወደ ፡ ሕይወትም ፡ ይሻገራል
በመድኃኒታችን ፡ ቃል
ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ ሲል ፡ ይጠራናል
ድምጹ ፡ ለሁላችንም ፡ ይሰማናል
ለጠፋው ፡ ልጅ ፡ አባቱ ፡ ተመለስ ፡ ይለዋል
እኛንም ፡ ይጠብቃል