የመስቀል ፡ ውርደት ፡ ስድብም (Yemesqel Wurdet Sidibm)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የመስቀል ፡ ውርደት ፡ ስድብም
ተሸከምህልን ፡ ጌታ
የጠፉትን ፡ ለማዳንም
ሞትህልን ፡ በጐልጐታ
ኦ! ፍቅር ፡ ግሩም
ኦ! ቅዱስ ፡ ደም
ስለእኛ ፡ የተሰጠ

የመስቀል ፡ ሸክም ፡ ከባድ ፡ ነው
የእኛ ፡ ዕዳ ፡ ሲጨመር
ምሥጋና ፡ ከማይሰጥህ ፡ ሰው
እኛ ፡ እንዳንደመር
አስታውሰን
ሙቅ ፡ ፍቅርህን
ልባችንን ፡ የሚሰብር

የመስቀል ፡ መንገድ ፡ መረጥህ
ትተህ ፡ የአባትህ ፡ ግርማ
ልታስረዳን ፡ ታላቅ ፡ ፍቅርህ
ተዋረድህ ፡ ስለእኛ
ይታገሣል
ያሸንፋል
ኦ! ጌታ ፡ የአንተ ፡ ፍቅር

በመስቀልህ ፡ ሥቃይ ፡ ጌታ
ሞትን ፡ ያስወገድህልን
እኛ ፡ ድል ፡ ነሥተን ፡ በደስታ
ቤትህን ፡ መግባት ፡ አስችለን
በአንተ ፡ ዕምነት
ለነፍስ ፡ ዕረፍት
አሁን ፡ በጻማህ ፡ አለን