የምሥጋና ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ለእኛ ፡ ዛሬ (Yemesgana Qen New Legna Zarie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search


1) በወጀብ ፡ ባውሎ ፡ ንፋስ ፡ ውስጥ ፡ ስንጐሽም ፡ ስንገፋ
ደረሰልን ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ታዳጊው ፡ የእሥራኤል ፡ ተስፋን
ሞገዱንም ፡ ገሰጸልን ፡ ማዕበሉንም ፡ ጸጥ ፡ አረገው
እልል ፡ እንበል ፡ እናመስግን ፡ ዛሬ ፡ የደስታችን ፡ ቀን ፡ ነው ።
 
አዝ፦ የምሥጋና ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ለእኛ ፡ ዛሬ
የአዲስ ፡ ቅኔ ፡ የዝማሬ
ኑ ፡ እናመስግን ፡ ጌታ ፡ አምላካችንን
ሰርቶልናልና ፡ ስራችንን (፪x)

2) ከአቅማችን ፡ በላይ ፡ ከብዶን ፡ የሚረዳን ፡ ወገን ፡ አጥተን
ረዴታችን ፡ መጣልን ፡ የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ አሰበን
በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ በዝማሬ ፡ በከበሮ ፡ እናስተጋባ
ሥራችንን ፡ ሠርቶልናል ፡ ምሥጋናችንን ፡ እናግባ

አዝ፦ የምሥጋና ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ለእኛ ፡ ዛሬ
የአዲስ ፡ ቅኔ ፡ የዝማሬ
ኑ ፡ እናመስግን ፡ ጌታ ፡ አምላካችንን
ሰርቶልናልና ፡ ስራችንን (፪x)

3) ቁጣው ፡ ነዶ ፡ በላያችን ፡ የተመኘው ፡ ለሞታችን
በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ ገባ ፡ አመጸኛው ፡ ጠላታችን
ስለዚህ ፡ እንውጣ ፡ ዛሬ ፡ በእልልታ ፡ እየዘመርን
እስትንፋስ ፡ ያላችሁ ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔርን ፡ እናመስግን ።

አዝ፦ የምሥጋና ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ለእኛ ፡ ዛሬ
የአዲስ ፡ ቅኔ ፡ የዝማሬ
ኑ ፡ እናመስግን ፡ ጌታ ፡ አምላካችንን
ሰርቶልናልና ፡ ስራችንን (፪x)