የምሥጋና ፡ ነዶ (Yemesgana Nedo)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ የምሥጋና ፡ ነዶ ፡ እወዘውዛለሁ
እንደ ፡ ሰባ ፡ እንቦሳ ፡ በፊህ ፡ እዘላለሁ
ክብር ፡ ይገባሃል ፡ እሰግድልሃለሁ
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ እቀኝልሃለሁ

የመዳኔ ፡ አለት ፡ የሕይወቴ ፡ ብርሃን
የሰላሜ ፡ ጌታ ፡ የኑሮዬ ፡ መቃን
ጐጆዬ ፡ ትዳሬ ፡ አለኝታዬ ፡ ቅርሴ
ልበልህ ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱሴ

አዝ፦ የምሥጋና ፡ ነዶ ፡ እወዘውዛለሁ
እንደ ፡ ሰባ ፡ እንቦሳ ፡ በፊህ ፡ እዘላለሁ
ክብር ፡ ይገባሃል ፡ እሰግድልሃለሁ
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ እቀኝልሃለሁ

የታሰርኩበት ፡ ትብታቡን ፡ በጣጥሰህ
የተቆፈረውን ፡ መቃብሬን ፡ ደፍነህ
የአውሬውን ፡ መንጋጋ ፡ አፉን ፡ ዘጋህልኝ
ይኸው ፡ ለምሥጋና ፡ ለዚህ ፡ አበቃኸኝ

አዝ፦ የምሥጋና ፡ ነዶ ፡ እወዘውዛለሁ
እንደ ፡ ሰባ ፡ እንቦሳ ፡ በፊህ ፡ እዘላለሁ
ክብር ፡ ይገባሃል ፡ እሰግድልሃለሁ
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ እቀኝልሃለሁ

ለነበረኝ ፡ ላለኝ ፡ ለሚኖረኝ ፡ ሁሉ
ለንብረት ፡ ለዕድሜ ፡ ለፀጋህ ፡ በሙሉ
ተመጣጣኝ ፡ ዋጋ ፡ ምን ፡ እከፍልሃለሁ
ምሥጋና ፡ ሰውቼ ፡ እስከብርሃለሁ

አዝ፦ የምሥጋና ፡ ነዶ ፡ እወዘውዛለሁ
እንደ ፡ ሰባ ፡ እንቦሳ ፡ በፊህ ፡ እዘላለሁ
ክብር ፡ ይገባሃል ፡ እሰግድልሃለሁ
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ እቀኝልሃለሁ

ከሙታን ፡ ማደሪያ ፡ ከመቃብር ፡ ዓለም
ተመስገን ፡ እያለ ፡ የሚያከብርህ ፡ የለም ፡
እንኔ ፡ ግን ፡ ከሞት ፡ አፍ ፡ ከሲኦል ፡ አምልጬ
ሕያው ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ፡ በአንተ ፡ ተመርጬ

አዝ፦ የምሥጋና ፡ ነዶ ፡ እወዘውዛለሁ
እንደ ፡ ሰባ ፡ እንቦሳ ፡ በፊህ ፡ እዘላለሁ
ክብር ፡ ይገባሃል ፡ እሰግድልሃለሁ
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ እቀኝልሃለሁ