የማይተወኝ ፡ ቸር ፡ ወዳጄ (Yemaytewegne Cher Wodajie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የማይተወኝ ፡ ቸር ፡ ወዳጄ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው
እኔም ፡ እንዴት ፡ እርሱን ፡ ክጄ
ወዳጅነቱን ፡ ልተው
እስከዚህ ፡ ድረስ ፡ ሲወደኝ
አንዳችም ፡ አይለየኝም
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አንድነት ፡ አለኝ
ዛሬና ፡ ዘለዓለም

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ከሞተልኝ
ማንም ፡ አይፈርድብኝም
ከአባቱም ፡ ሲለምንልኝ
ፀጋው ፡ አይቀርብኝም
ጠበቃዬም ፡ ሲሆንልኝ
ማን ፡ ሊከሰኝ ፡ ይችላል?
በከሃሊ ፡ እጁም ፡ ሲይዘኝ
ከእርሱ ፡ ማን ፡ ይነጥቀኛል?

ሕይወትና ፡ ሞት ፡ ከኢየሱስ
እንዳይለየኝ ፡ አመንሁ
ልቤም ፡ በፍርሃት ፡ ሲደቆስ
ኢየሱስን ፡ ተማጠንሁ
ውርደትም ፡ ቢሆን ፡ ወይም ፡ ክብር
ደስታም ፡ ሆነ ፣ ሃዘንም
በእርሱ ፡ ካለኝ ፡ ከአምላክ ፡ ፍቅር
ከቶ ፡ አያወጣኝም ።