የማይነገር ፡ ነው ፡ የማይታሰብ ፡ ነው (Yemayneger Niew Yemaytaseb Niew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የማይነገር ፡ ነው ፣ የማይታሰብ ፡ ነው
ታላቅ ፡ ደስታ ፡ የልደት ፡ ቀን
አቅርቡ ፡ ክብር ፡ በሁሉ ፡ ምድር
ያምላክን ፡ ፍቅር ፡ እናመስግን

መሢሑ ፡ መጣልን ፣ ሕዝቡን ፡ ሊያድን
ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ ከእሤይ ፡ ሥር
ዕርቅን ፡ አመጣ ፡ ተገኘ ፡ ነጻ
ሐሤትን ፡ አድርጊ ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ

አምላክ ፡ ይመስገን ፡ ስለሚሰጠን
ፀጋ ፡ ሁሉ ፡ በቸር ፡ ልጁ
ወንድም ፡ ሆነልን ፣ ደጅ ፡ ከፈተልን
ልጆች ፡ ሲለነ ፡ ሰዎች ፡ ሁሉ