የልብህን ፡ በር ፡ የሚመታ ፡ ማን ፡ ነው (Yelibihin Ber Yemimeta Man Niew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የልብህን ፡ በር ፡ የሚመታ ፡ ማን ፡ ነው?
ማን ፡ ይጠራል?
በደሙ ፡ የገዛህ ፡ መድኃኒትህ ፡ ነው
በፍቅሩ ፡ ለኣንተም ፡ ይራራል

በፊትም ፡ ሲጠራህ ፡ ሲፈልግህም
ሰምተሃል ፡ ወይ?
ለጌታህ ፡ ለርኅሩኅ ፡ መድኃኒትህም
የልብህን ፡ በር ፡ ከፍተሃል ፡ ወይ?

የዓለም ፡ ከንቱነት ፡ የልብህን ፡ ራብ
አያርቅም
ወዳለምም ፡ ደስታ ፡ ፈቃድህ ፡ ሲሳብ
መባባት ፡ ከልብህ ፡ አይለቅም

የዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ብልፅግና ፣ ከብት
ብትወርስም
በምድሩ ፡ ብቻ ፡ ካገኘኸው ፡ ሃብት
ሰላም ፡ ወደ ፡ ልብህ ፡ አይደርስም

በሰው ፡ ወዳጅነት ፡ በዓለምም ፡ ሸር
ብትመራ
ረድዔት ፡ ስጽሃ ፡ ሳታገኝ ፡ ብትቀር
ያጋልጡሃል ፡ ስትጠራ

ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ቢሰጥህ ፣ የዕውነት ፡ ሰላም
ለዘለዓለም
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ሃብት ፡ አትሻም
አይተውህምም ፡ በዚህ ፡ ዓለም

የኢየሱስ ፡ ወዳጅ ፡ ከመሆን ፡ የሚበልጥ
ምን ፡ ይገኛል?
የፍቅሩን ፣ የፀጋውንም ፡ መብለጥ ፡ ሲገልጥ
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ያስመኛል?

ብፅዕናን ፡ ሊሰጥህ ፡ ለመጣው ፡ ወዳጅ
ክፈትለት
ለአንተም ፡ ብፅዕናህን ፡ ሲያዘጋጅ
የሰጠህን ፡ ተቀበልለት