From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
የልደት ፡ ማታ ፡ እንዴት ፡ ያበራል
መብራት ፡ ሲለኮስ ፡ በልብና ፡ ቤት
የመላእክት ፡ መዝሙር ፡ አሁን ፡ ይሰማል
ከጥንቱ ፡ ጀምሮ ፡ ይደወላል
ለአምላክ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና ፡ በምድርም ፡ ሰላም
ለሰው ፡ በጐ ፡ ፈቃድ ፡ ይሁን ፡ ሲሉ ፡ ዘመሩ
የልደት ፡ ማታ ፡ እንዴት ፡ ያበራል
መብራት ፡ ሲለኮስ ፡ በልብና ፡ ቤት
አምላክ ፡ ለምድር ፡ የሰጠው ፡ ስጦታ
ለኃጢአተኞች ፡ መዳን ፡ ይሆናል
ፀሐይ ፡ በዓለም ፡ እንደሚወጣ
ጨለማን ፡ ኢየሱስ ፡ አሸንፏል
ሕዝብ ፡ በጨለማ ፡ የሄደ ፡ በሞት ፡ አገርም
በጽላም ፡ የኖረ ፡ ሕዝብ ፡ ታላቅ ፡ ብርሃን ፡ አየ
አምላክ ፡ ለምድር ፡ የሰጠው ፡ ስጦታ
ለኃጢአተኞች ፡ መዳን ፡ ይሆናል
በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው ፡ የተሰጠ
እርቅና ፡ ጽድቅ ፡ ሕይወትና ፡ ሰላም
መድኃኒታችን ፡ የወይን ፡ ዛፍ ፡ ሆነ
የሕይወት ፡ ፍሬ ፡ ከእርሱ ፡ አገኘነ
አንድ ፡ ወንድ ፡ ፍሬ ፡ ተሰጠነ ፡ ህፃን ፡ ተወልዷል
አለቅነቱም ፡ በጫንቃው ፡ ላይ ፡ ይሆናል
በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው ፡ የተሰጠ
እርቅና ፡ ጽድቅ ፡ ሕይወትና ፡ ሰላም
|