From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ የክብር ፡ መንፈስ ፡ የክብር ፡ መንፈስ
በአርያም ፡ ያለው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መቅደስ
የክብር ፡ መንፈስ ፡ በእኛም ፡ ላይ ፡ ይፍሰስ
በእሣት ፡ ቁጥቋጦ ፡ ውስጥ ፡ ሙሴን ፡ ያናገርከው
የመላዕክትን ፡ ምግብ ፡ ለሕዝብህ ፡ ያደልከው
ስማን ፡ ጩኸታችንን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ተነሥ
በኢትዮጵያ ፡ ምድር ፡ የድል ፡ መንፈስ ፡ አፍስስ
አዝ፦ የክብር ፡ መንፈስ ፡ የክብር ፡ መንፈስ
በአርያም ፡ ያለው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መቅደስ
የክብር ፡ መንፈስ ፡ በእኛም ፡ ላይ ፡ ይፍሰስ
ሰለሞን ፡ መቅደሱን ፡ ሠርቶ ፡ እንደጨረሰ
በደመና ፡ ክብር ፡ ከሰማይ ፡ ፈሰሰ
ልመናችንን ፡ ስማን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ! ተነሥ
እኛን ፡ ተናገረን ፡ መንፈስህን ፡ አፍስስ
አዝ፦ የክብር ፡ መንፈስ ፡ የክብር ፡ መንፈስ
በአርያም ፡ ያለው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መቅደስ
የክብር ፡ መንፈስ ፡ በእኛም ፡ ላይ ፡ ይፍሰስ
አጋንንቶች ፡ ይውጡ ፡ ስማቸው ፡ ይደምሰስ
ሽባዎች ፡ ይነሡ ፡ ድውዩም ፡ ይፈወስ
ጠላት ፡ ሲወድቅ ፡ እንይ ፡ በሰይፍ ፡ ሲወጋ
በጠራሃቸው ፡ ፊት ፡ የክብር ፡ እጅህን ፡ ዘርጋ
አዝ፦ የክብር ፡ መንፈስ ፡ የክብር ፡ መንፈስ
በአርያም ፡ ያለው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መቅደስ
የክብር ፡ መንፈስ ፡ በእኛም ፡ ላይ ፡ ይፍሰስ
ስምህን ፡ እንጠራለን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ! መልስ
በጉባዔ ፡ መሃል ፡ ክብርህ ፡ ይመላለስ
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ስማን ፡ ልመናችንን
በከበረው ፡ መንፈስ ፡ ጐብኛት ፡ አገራችንን
አዝ፦ የክብር ፡ መንፈስ ፡ የክብር ፡ መንፈስ
በአርያም ፡ ያለው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መቅደስ
የክብር ፡ መንፈስ ፡ በእኛም ፡ ላይ ፡ ይፍሰስ
እንደ ፡ ቀድሞ ፡ ሕዝብህ ፡ ጌታ ፡ ስማንና
ባሪያህን ፡ አስነሣው ፡ ይስሐቅን ፡ ቀባና
ጴጥሮስ ፡ ቢሆን ፡ ጳውሎስ ፡ ሙሴ ፡ ወይ ፡ ኢያሱ
አንተ ፡ ለፈቀድከው ፡ እግዚአብሔር ፡ ቅባልን
አዝ፦ የክብር ፡ መንፈስ ፡ የክብር ፡ መንፈስ
በአርያም ፡ ያለው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መቅደስ
የክብር ፡ መንፈስ ፡ በእኛም ፡ ላይ ፡ ይፍሰስ
|