From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ ፣
የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ስሙም ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ
ትላንት ፡ የነበረው ፡ ታላቅ ፡ ኃይሉ
ዛሬም ፡ ይሠራል ፡ በዓለም ፡ ሁሉ
እንመካለን ፡ በጌታችን
ሲሠራ ፡ አይተናል ፡ በዓይናችን
አዝ ፣
የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ስሙም ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ
የጠላትን ፡ በር ፡ ጥሶ ፡ ገብቶ
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ በእኛ ፡ ዘርቶ
አዲስ ፡ አረገኝ ፡ እንደራሱ
ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ
አዝ ፣
የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ስሙም ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ
ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ የማይሻር
ክንዱም ፡ ጠንካራ ፡ የማይበገር
የሆነው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የማይረታ
አዝ ፣
የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ስሙም ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ
የድሉ ፡ ጌታ ፡ ጌታችን ፡ ነው
እናምነዋለን ፡ ስሙም ፡ ይኸው
ላንክደው ፡ ቃል ፡ ገብተናል
አንዋሽም ፡ ክንዱን ፡ አይተናል
አዝ ፣
የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ስሙም ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ
|