የሕይወትን ፡ ምንጭ ፡ አየሁ (Yehiwoten Mench Ayehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የሕይወትን ፡ ምንጭ ፡ አየሁ
ሲወጣ ፡ ከጐኑ
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ የታጠቡ
ከኃጢአት ፡ ይነፃሉ
ከኃጢአት ፡ ይነፃሉ (፪x)
 
ያ ፡ ሕያው ፡ ምኝጭ ፡ ያነፃኛል
ከሠራሁት ፡ በደል
እቀበላለሁ ፡ በምሕረት
የኃጢአቴን ፡ ሥርየት
የኃጢአቴን ፡ ሥርየት (፪x)

ያንን ፡ ምንጭ ፡ ካየሁ ፡ በዕምነት
እድናለሁ ፡ ከሞት
አምላክ ፡ በፍቅሩ ፡ ብቻ ፡ ነው
ሰውን ፡ ሁሉ ፡ ያዳነው
ሰውን ፡ ሁሉ ፡ ያዳነው (፪x)

በሰማያት ፡ አዲስ ፡ መዝሙር
ልዘምር ፡ ለርሱ ፡ ክብር
ላነፃኝ ፡ በምሕረቱ
ላገባኝ ፡ በቤቱ
ላገባኝ ፡ በቤቱ (፪x)