የሕይወት ፡ እንጀራ (Yehiwot Enjera)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ ቁረስልኝ
በባሕር ፡ ዳር ፡ ምግብ ፡ እንደቆረስህ
በተቀደሰው ፡ ገጽ ፡ እሻሃለሁ
መንፈሴ ፡ ናፍቆሃል ፡ ሕያው ፡ ቃል ፡ ሆይ !
እውነቱን ፡ ባርክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ
በገሊላ ፡ ምግብ ፡ እንደባረክህ
ነጻ ፡ እወጣለሁ ፡ ከእሥራቴ
ሰላም ፡ አገኛለሁ ፡ በሙልዓቴ
መንፈስን ፡ ላክልኝ ፡ አሁን ፡ ለእኔ
ዓይኔን ፡ እንዲነካኝ ፡ እንዲያሳየኝ
ከቃልህ ፡ እውነቱን ፡ ግለጽልኝ
በመጽሐፍህ ፡ እንዳይህ ፡ አድርገኝ
የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
የቅዱሱ ፡ ቃልህ ፡ መዳኛዬ
በልቼው ፡ እንድኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
እውነትህን ፡ አስታውቀኝ ፡ ፈቅር ፡ አምላክ
|