ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ (Yehen Yekeber Semehen Letra)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ስምህን ፡ ጠርቼ ፡ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት
ከእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ለእኛ ፡ ተሰጥተህ ፡ የሆንክልን ፡ ልዩ ፡ በረከት
ከሠማይ ፡ በታች ፡ አዳኛችን ፡ ሆኖ ፡ ተሰጥቶናልና
ሁሉን ፡ ማድረግ ፡ የሚችለውን ፡ ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ

አዝይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ (፫x)
ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ

2. የሰይጣንን ፡ ምሽግ ፡ የሚንድ ፡ ኃያል ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ታላቅ ፡ ስም
በደዌ ፡ ሁሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው ፡ ዲዳን ፡ ለማናገር ፡ የሚችል
ሽባ ፡ አዘልሎ ፡ ለምጽ ፡ አንጽቶ ፡ ነጻነት ፡ የሚሰጥ ፡ ነውና
ስለዚህ ፡ ምሥጋና ፡ ልሰዋ ፡ ይህን ፡ የክብር ፡ ስም ፡ ልጥራ

አዝይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ (፫x)
ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ

3. በሠማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ስምህ ፡ በሁሉም ፡ ላይ ፡ ስልጣን ፡ ያለው
ይህንን ፡ አታደርግም ፡ ብሎ ፡ የሚቋቋመው ፡ ኃይል ፡ የለም
በዓለም ፡ ላይ ፡ ተወዳዳሪ ፡ ፍፁም ፡ አቻ ፡ የለውምና
ስለዚህ ፡ እስቲ ፡ ላመስግንህ ፡ ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ

አዝይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ (፫x)
ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ

4. ጋሻ ፡ ነው ፡ ለሚታመኑበት ፡ ምሽግ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ መጠለያ
ሰይጣንን ፡ የሚያስጐበድድ ፡ ጦር ፡ ነው ፡ የሚሆን ፡ ለመዋጊያ
ያንተን ፡ ስም ፡ ጠርቶ ፡ ያፈረ ፡ ፍፁም ፡ አልተገኘምና
ይክበር ፡ ብሩክ ፡ ይሁን ፡ እያልኩኝ ፡ ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ

አዝይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ (፫x)
ይህን ፡ የክብር ፡ ስምህን ፡ ልጥራ