From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ይኸ ፡ ቤት ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ስፍራውም ፡ ያንተ ፡ ነው
እኛም ፡ ያንተው ፡ ነን ፡ ጊዜውም ፡ ያንተው ፡ ነው
ሁሉን ፡ ሰጥተንሃል ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘህ ፡ አድርገው
1. ፈውስ ፡ የሚያስፈልገው ፡ ህመምተኛም ፡ አለ
በዲያቢሎስ ፡ ውጊያ ፡ ልቡ ፡ የቆሰለ
ያለውን ፡ አራግፎ ፡ ባዶውን ፡ የመጣ
ከአንተ ፡ የሚጠብቅ ፡ ስለማይታጣ
በባሪያዎችህ ፡ አፍ ፡ በረከትህ ፡ ይፍሰስ
ጌታ ፡ በዚህ ፡ መሃል ፡ ክብርህ ፡ ይመላለስ (፪x)
አዝ፦ ይኸ ፡ ቤት ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ስፍራውም ፡ ያንተ ፡ ነው
እኛም ፡ ያንተው ፡ ነን ፡ ጊዜውም ፡ ያንተው ፡ ነው
ሁሉን ፡ ሰጥተንሃል ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘህ ፡ አድርገው
2. በሰለሞን ፡ መቅደስ ፡ ታቦትን ፡ ባለበት
የክብር ፡ መንፈስህ ፡ እንዲፈስበት
ደግሞም ፡ በደመና ፡ ዙሪያውን ፡ እንዳጠርክ
ዛሬም ፡ በዚያ ፡ ኃይልህ ፡ ይህንን ፡ ቢት ፡ ባርከው
በዘርፋፋ ፡ ልብስህ ፡ ግባ ፡ እለፍበት
ዛሬም ፡ በዚህ ፡ ቤት ፡ ላይ ፡ ኃይልህ ፡ ይረፍበት (፪x)
አዝ፦ ይኸ ፡ ቤት ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ስፍራውም ፡ ያንተ ፡ ነው
እኛም ፡ ያንተው ፡ ነን ፡ ጊዜውም ፡ ያንተው ፡ ነው
ሁሉን ፡ ሰጥተንሃል ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘህ ፡ አድርገው
3. የቀራንዮ ፡ ፍቅርህ ፡ ጠርቶ ፡ ሰብስቦናል
በዚህ ፡ ልንከማች ፡ ምክንያት ፡ ሆኖናል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ እንጂ ፡ ሰው ፡ አይናገረን
የሁላችን ፡ ዐይን ፡ ወደአንተ ፡ ነውና
አጽናናን ፡ በቃልህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ና (፪x)
አዝ፦ ይኸ ፡ ቤት ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ስፍራውም ፡ ያንተ ፡ ነው
እኛም ፡ ያንተው ፡ ነን ፡ ጊዜውም ፡ ያንተው ፡ ነው
ሁሉን ፡ ሰጥተንሃል ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘህ ፡ አድርገው
|