የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ (Yegna Gieta Yegna Eyesus)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ሥሙ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ

ትላንት ፡ የነበረው ፡ ታላቅ ፡ ኃይሉ
ዛሬም ፡ ይሠራል ፡ በዓለም ፡ ሁሉ
እንመካለን ፡ በጌታችን
ሲሰራ ፡ አይተናል ፡ በዓይናችን

አዝ፦ የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ሥሙ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ

የጠላትን ፡ በር ፡ ጥሶ ፡ ገብቶ
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ በእኛ ፡ ዘርቶ
አዲስ ፡ አደረገን ፡ እንደራሱ
ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ

አዝ፦ የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ሥሙ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ

ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ የማይሻር
ክንዱም ፡ ጠንካራ ፡ የማይበገር
የሆነው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የማይረታ

አዝ፦ የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ሥሙ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ

የድሉ ፡ ጌታ ፡ ጌታችን ፡ ነው
እናምነዋለን ፡ ስሙም ፡ ይኸው
ላንክደው ፡ ቃል ፡ ገብተናል
አንዋሽም ፡ ክንዱን ፡ አይተናል

አዝ፦ የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አዲስ
ሥሙ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሚፈውስ