ይገባሃል ፡ ምሥጋና (Yegebahal Mesgana)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ
አምላካችን ፡ ይገባሃል ፡ ምሥጋና (፬x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ጅማሬ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜም ፡ የለህም
ያለህ ፡ የነበርህ ፡ ነህ ፡ ደግሞም ፡ ትኖራለህ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ

1. ባሕር ፡ ውቅያኖስን ፡ ትቆጣጠራለህ
የብሱን ፡ ሠማዩንም ፡ ሁሉን ፡ ትገዛለህ
ስራህ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ የለም ፡ የሚሳንህ
በዕውቀት ፡ ትመራለህ ፡ ሁሉንም ፡ በኃይልህ

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ
አምላካችን ፡ ይገባሃል ፡ ምሥጋና (፬x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ጅማሬ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜም ፡ የለህም
ያለህ ፡ የነበርህ ፡ ነህ ፡ ደግሞም ፡ ትኖራለህ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ

2. በዘመናት ፡ ሁሉ ፡ ዕውቀትህ ፡ አይቀንስ
ጥበብህ ፡ አይጐድል ፡ ኃይልህ ፡ ከቶ ፡ አያንስ
ሁሉን ፡ ቻይነትህ ፡ ብርቱውን ፡ አሳፍሯል
እጁን ፡ በአፉ ፡ ላይ ፡ ስንቱ ፡ ጠቢብ ፡ ጭኗል

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ
አምላካችን ፡ ይገባሃል ፡ ምሥጋና (፬x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ጅማሬ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜም ፡ የለህም
ያለህ ፡ የነበርህ ፡ ነህ ፡ ደግሞም ፡ ትኖራለህ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ

3. ጥንት ፡ በአባቶቻችን ፡ ድንቅን ፡ እንደሰራህ
ደግሞም ፡ በዚህ ፡ ትውልድ ፡ ስምህን ፡ አስጠራህ
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ ስምህ ፡ ሰዎችን ፡ ፈወሰ
ወደአንተ ፡ የመጡትን ፡ በሙሉ ፡ ዳሰሰ

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ
አምላካችን ፡ ይገባሃል ፡ ምሥጋና (፬x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ጅማሬ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜም ፡ የለህም
ያለህ ፡ የነበርህ ፡ ነህ ፡ ደግሞም ፡ ትኖራለህ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ

4. ስምህ ፡ አቻ ፡ የለው ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ይሰራል
በታላቅ ፡ ስልጣኑ ፡ ተዐምራት ፡ ያደርጋል
ሙታንን ፡ ያስነሳል ፡ ሕይወት ፡ ይለውጣል
ሳያረጅ ፡ ሳይደክም ፡ ዘለዓለም ፡ ይኖራል

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ
አምላካችን ፡ ይገባሃል ፡ ምሥጋና (፬x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ጅማሬ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜም ፡ የለህም
ያለህ ፡ የነበርህ ፡ ነህ ፡ ደግሞም ፡ ትኖራለህ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ