የደስታ ፡ ዘመን ፡ ሆኗል (Yedesta Zemen Honoal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የደስታ ፡ ዘመን ፡ ሆኗል
ክርስቶስ ፡ አሁን ፡ ድል ፡ ነሥቷል
ሲነሣም ፡ ከመቃብሩ
ታየልን ፡ አምላክነቱ

ከመቅሠፍትም ፡ ሊያድነን
በሞተ ፡ በሦስተኛው ፡ ቀን
ተነሥቶ ፡ ደግሞ ፡ እንዲያርግ
ተጽፎ ፡ ነበር ፡ በአምላክ ፡ ሕግ

ቢጠብቁም ፡ መቃብሩን
ወጣበት ፡ ጥሶ ፡ ድንጋዩን
የሕይወት ፡ ንጉሥም ፡ ቢሞት
አልቀረም ፡ በሲዖል ፡ ግዞት

ሲዖል ፡ አሁን ፡ ተሸነፈ
የሞትም ፡ ገዧ ፡ ተቀሠፈ
ሃሌ ፡ ሉያ ! ተነሥቷል
ጌታችን ፡ እንደ ፡ ተስፋው ፡ ቃል

ከሞት ፡ ሥልጣን ፡ ያወጣኸን
ኦ! ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ተመስገን
ጻድቃን ፡ በሚነሡበት ፡ ቀን
የሕይወት ፡ ትንሣዔ ፡ ስጠን