የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ (Yebelay Neh Gieta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከአንተ ፡ ጋር ፡ የሚቆም ፡ ደፍሮ ፡ የሚወዳደር ፡ የበላይ ፡ የበላይ
አልተገኘም ፡ በምድር ፡ ከጫፍ ፡ ጫፍ ፡ ቢቆጠር ፡ የበላይ ፡ የበላይ
ስምህ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ስራህ ፡ ይናገራል ፡ የበላይ ፡ የበላይ
የትኛው ፡ ጀግና ፡ ሰው ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሏል ፡ የበላይ ፡ የበላይ

የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ
በላይ ፡ በላይ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ
የበላይ ፡ የሁለ ፡ በላይ (፬x)

አዝ፦ ኦ ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ሃሌሉያ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ ለሆነው ፡ አንበሳ ፡ ለሌለው ፡ አምሳያ
ልበል ፡ ላመስግንህ ፡ ከአንጀቴ
ውለታው ፡ ስለበዛ ፡ የመድኃኒቴ

ሳላውቀው ፡ ያወቀኝ ፡ ሳልሻው ፡ ያዳነኝ
በአስገራሚ ፡ ፍቅሩ ፡ እኔን ፡ የወደደኝ
ከጥፋት ፡ እሩጫ ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ኢየሱስ ፡ ነውና ፡ ያወጣኝ ፡ ከእሳት

አዝ፦ ኦ ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ሃሌሉያ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ ለሆነው ፡ አንበሳ ፡ ለሌለው ፡ አምሳያ
ልበል ፡ ላመስግንህ ፡ ከአንጀቴ
ውለታው ፡ ስለበዛ ፡ የመድኃኒቴ

እግዚአብሔር ፡ የሚበልጥ ፡ አንድም ፡ ነገር ፡ አላውቅም
ይህ ፡ እንደዚህ ፡ ነው ፡ እንደዚያ ፡ ነው ፡ አልልም
ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ
የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ከዚህ ፡ ሁለ ፡ በላይ ፡ ነው
የበላይ ፡ የበላይ ፡ ነህ ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ ነህ