የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ (Yeaddis Kidan Beg)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከብዶን ፡ የነበረውን ፡ የሕግ ፡ ጭነት
ፍጥረትን ፡ ሲያስጨንቅ ፡ ስለ ፡ ኃጢአት
የህዝብህን ፡ ኃጢአት ፡ አንዴ ፡ ለማስቀረት
ኢየሱስ ፡ ሕይወቱን ፡ ሰጠ ፡ ለመስቀል ፡ ስቅላት

አዝ፦ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ቅዱስ ፡ ካህን
የፅድቅ ፡ ንጉሥ ፡ የዓለም ፡ መድኅን
የእውነተኛይቱ ፡ ድንኳን ፡ አገልጋይ
ቅዱስ ፡ ካህን ፡ አለን ፡ በሰማይ (፪x)

የኃጢአት ፡ መጋረጃ ፡ እኛን ፡ የለየን
ኢየሱስ ፡ ተረተረው ፡ መሥዋዕት ፡ ሆኖልን
ቅድስተ ፡ ቅዱሣን ፡ የተስፋው ፡ አገር
በእርሱ ፡ ልንገባ ፡ ቻልን ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ በር

አዝ፦ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ቅዱስ ፡ ካህን
የፅድቅ ፡ ንጉሥ ፡ የዓለም ፡ መድኅን
የእውነተኛይቱ ፡ ድንኳን ፡ አገልጋይ
ቅዱስ ፡ ካህን ፡ አለን ፡ በሰማይ (፪x)

የኮርማ ፡ ደም ፡ መሥዋዕት ፡ ለእኛ ፡ አያስፈልገንም
አንዴ ፡ ተረጭተናል ፡ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም
ቅዱስ ፡ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ መካከለኛው
ነፍሱን ፡ ወዶ ፡ ሰጠ ፡ ለሞት ፡ ስለ ፡ እኛ

አዝ፦ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ቅዱስ ፡ ካህን
የፅድቅ ፡ ንጉሥ ፡ የዓለም ፡ መድኅን
የእውነተኛይቱ ፡ ድንኳን ፡ አገልጋይ
ቅዱስ ፡ ካህን ፡ አለን ፡ በሰማይ (፪x)