የክርስቶስ ፡ የአምላካችን ፡ ሞት (YeKristos YeAmlakachin Mot)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የክርስቶስ ፡ የአምላካችን ፡ ሞት
ለመንፈሣችን ፡ ነው ፡ ሕይወት
ለልቦናችንም ፡ ሰላም
አግኝተናል ፡ ከእርሱ ፡ ሕማም

የክርስቶስ ፡ ደም ፡ ከፈሰሰ
ዕዳችን ፡ ተደመሰሰ
አጥብቆ ፡ ስለወደደን
ከአምላክ ፡ ጋር ፡ አስታረቀን

ይህንን ፡ እንድናምነው
ፀጋውን ፡ እንድንቀበለው
ቅዱስ ፡ መያዣ ፡ ሰጥቶናል
ቁርባኑንም ፡ ሠርቶልናል

አሁን ፡ ሥጋውን ፡ ያበላናል
በማዕዱም ፡ ያጠጣናል
ያንን ፡ የፈሰሰልን ፡ ደም
ሲያይ ፡ ይሰጣል ፡ ፅድቁንም

ይህ ፡ ሰማያዊ ፡ መና ፡ ነው
ይህ ፡ የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ ነው
ያን ፡ ሕብሥት ፡ ስንቀበልም
ዘላለም ፡ አያልቅብንም