የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ያጸናናል (YeEyesus Sim Yatsenanal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ያጸናናል
በመከራም ፡ ይረዳናል
በኢየሱስ ፡ ፀጋ ፡ አለነ
የዓብ ፡ ሥምረትን ፡ ሰጠነ

ኦ! የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ኦ! ረጃችን
በምሕረትህ ፡ ይቅር ፡ በለን
ሰው ፡ ነህ ፡ በዕውነት ፡ አምላክም
እይ ፡ ጭንቃችንን ፣ እርዳንም

ጽድቅ ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
ሰላምም ፡ ዕርቅም ፡ ከአንተ ፡ ነው
በቅዱስ ፡ ስምህ ፡ ያመነ
እርሱ ፡ ከሁሉ ፡ ፍርድ ፡ ዳነ

ምሥጋና ፡ ስለ ፡ ጥምቀትህ
ስለ ፡ ቁርባንም ፡ እንስጥህ
በዚህ ፡ ሕይወት ፡ ሰላም ፡ ስጠን
ወደ ፡ ሰማይም ፡ ስብስበን