የኢየሱስ ፡ ልብ ፡ ተከፈተልህ (YeEyesus Lib Tekefetelih)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የኢየሱስ ፡ ልብ ፡ ተከፈተልህ
በምሕረቱም ፡ ይጠራሃል
የምስኪኑ ፡ ወዳጅ ፡ ራራልህ
መድኃኒትም ፡ ይሰጥሃል
ቃሉን ፡ አሁን ፡ ስታደምጸው
ልብህን ፡ አታደንዝዘው

አሁን ፡ ይጠራህል ፡ በፍቅር
አሁን ፡ መድኃኒታችን ፡ ነው
አንድ ፡ ቀን ፡ ግን ፡ መጥቶ ፡ በክብር
ሲጠራህ ፡ ፈራጃችን ፡ ነው
ዛሬ ፡ እርሱን ፡ ተቀብለህ
ለፍርድ ፡ ሲጠራህ ፡ ብፁዕ ፡ ነህ