የኢየሩሣሌም ፡ ልጆች ፡ ዘምሩለት (YeEyerusalem Lijoch Zemirulet)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የኢየሩሣሌም ፡ ልጆች ፡ ዘምሩለት
እኛም ፡ በየሥፍራችን ፡ እንደነርሱ ፡ ልንዘምር
ዘምሩ ፣ ስሙን ፡ አመስግኑ ፣ ዘምሩ ፡ ስሙን ፡ አመስግኑ ።
ሆሣዕና! ሆሣዕና! ሆሣዕና! ለዳዊት ፡ ልጅ ።

ዳዊት ፡ ንጉሥ ፡ ያለው ፡ ዕውነት ፡ ሆኖ ፡ ተገኘ
ከሕፃናት ፡ አፍ ፡ ደግሞ ፡ ምሥጋናን ፡ አዘጋጀሁ
ዘምሩ ፣ ስሙን ፡ አመስግኑ ፣ ዘምሩ ፡ ስሙን ፡ አመስግኑ ።
ሆሣዕና! ሆሣዕና! ሆሣዕና! ለዳዊት ፡ ልጅ ።

አምላክ ፡ አባታችን ፡ ነው ፡ መንገዱንም ፡ ሊመራን
ቅዱስ ፡ ቃሉ ፡ ሰጠነ ፡ ምሥጋናችን ፡ እናቅርብ
ዘምሩ ፣ ስሙን ፡ አመስግኑ ፣ ዘምሩ ፡ ስሙን ፡ አመስግኑ ።
ሆሣዕና! ሆሣዕና! ሆሣዕና! ለዳዊት ፡ ልጅ ።

ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ተነሡ ፡ ዘምሩለት ፡ ባንድነት
እስከ ፡ ሰማይ ፡ እንዲደርስ ፡ ድምፃችሁን ፡ ከፍ ፡ አድርጉ
ዘምሩ ፣ ስሙን ፡ አመስግኑ ፣ ዘምሩ ፡ ስሙን ፡ አመስግኑ ።
ሆሣዕና! ሆሣዕና! ሆሣዕና! ለዳዊት ፡ ልጅ ።