የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ የሚሽረው ፡ የለም (YeEgziabherin Qal Yemishirew Yelem)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ የሚሽረው ፡ የለም
እመሰክራለሁ ፡ በወንጌል ፡ አላፍርም
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ አባት ፡ ነው
ምሥክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪X)

በቀራንዮ ፡ ላይ ፡ የተሰቀለው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ለእኔም ፡ ለአንተም ፡ ነው
ደስታና ፡ ሰላም ፡ ፍቅር ፡ የሌለህ
ና ፡ ወደ ፡ አምላክህ ፡ ወደ ፡ ፈጠረህ

አዝ ፣
የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ የሚሽረው ፡ የለም
እመሰክራለሁ ፡ በወንጌል ፡ አላፍርም
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ አባት ፡ ነው
ምሥክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪X)

የሞት ፡ ጥላ ፡ ከቦህ ፡ ከሚያስጨንቅህ
ቅረብ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ዕረፍትን ፡ ይስጥህ
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ ይዳስስሃል
ፀጋውንም ፡ ሰጥቶ ፡ ይፈውስሃል

አዝ ፣
የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ የሚሽረው ፡ የለም
እመሰክራለሁ ፡ በወንጌል ፡ አላፍርም
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ አባት ፡ ነው
ምሥክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪X)

ኢየሱስ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የተከበረ
መች ፡ በአንተ ፡ ክኅደት ፡ ቃሎቹን ፡ ሻረ
ከሚነደው ፡ እሣት ፡ አንተን ፡ ሊያወጣህ
እጆቹን ፡ ዘርግቷል ፡ ፈጥኖ ፡ ሊያድንህ

አዝ ፣
የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ የሚሽረው ፡ የለም
እመሰክራለሁ ፡ በወንጌል ፡ አላፍርም
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ አባት ፡ ነው
ምሥክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪X)

ከያዘህም ፡ አዚም ፡ እንድትላቀቅ
በዕምነት ፡ ቅረብና ፡ በፀሎት ፡ ጠይቅ
እንደ ፡ አምላክህ ፡ ፈቃድ ፡ መኖር ፡ ስትጀምር
ይሳካልህማል ፡ ያሰብከው ፡ ነገር

አዝ ፣
የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ የሚሽረው ፡ የለም
እመሰክራለሁ ፡ በወንጌል ፡ አላፍርም
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ አባት ፡ ነው
ምሥክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪X)