From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
የአምላክ ፡ ፀጋ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ሰው ፡ የሆነውን ፡ ሁሉ ፡ ጠራ
ያለ ፡ ዕድልም ፡ ለሰው
በማይወሰን ፡ ምሕረት ፡ ራራ
ምሕረቱም ፡ ሲያድናቸው
የአዳም ፡ ልጆች ፡ እኩል ፡ ናቸው
ሁሉ ፡ ግፍ ፡ አደረጉ
ሁሉም ፡ ኃጢአትን ፡ ሠራ
አምላክን ፡ ሳይፈልጉ
ፅድቅን ፡ ሳያገኙም ፡ ቀሩ
ምኞትም ፡ በባሕሪያቸው
አንድ ፡ ሳይቀር ፡ አሸነፋቸው
ሁሉም ፡ እንደወደቁ
ሁሉም ፡ ኃጥአን ፡ እንደሆኑ
ሁሉ ፡ ደግሞ ፡ ጸደቁ
ሁሉም ፡ በአምላክ ፡ ፀጋ ፡ ዳኑ
ፀጋውም ፡ ብቻ ፡ ፅድቅ ፡ ሲሰጥም
ትምክሕት ፡ ለማንም ፡ የለም
በግዞት ፡ ቤት ፡ ታሥሮ
መቅሠፍት ፡ የተፈረደበት
መጽሐፍም ፡ ተምሮ
ዕውቀቱ ፡ የሚደምቅለት
ልዩነት ፡ ሳይኖር ፡ ሁለቱ
ይድናሉ ፡ በምሕረቱ
ፅድቅ ፡ የሹት ፡ ምዕመናን
ፍፁም ፡ ለአምላክ ፡ የተሰጡ
የተዋረዱም ፡ ኃጥአን
ወደ ፡ መስቀሉ ፡ ቢመጡ
ሳይለያዩ ፡ እኒህ ፡ ሁሉ
በአምላክ ፡ ፀጋ ፡ ይድናሉ
በክፋቱ ፡ አዝኖ
በምግባሩም ፡ የሚያፍር
ኃጢአቱን ፡ አምኖ
ፀጋን ፡ ማመን ፡ የማይደፍር
ራሱን ፡ ሊያጸድቅ ፡ ሲሞክር
ከንቱ ፡ ነው ፡ የልቡ ፡ ምክር
በሰው ፡ ጽድቅና ፡ ልፋት
የአምላክ ፡ ፀጋ ፡ አይሰናዳም
የሰው ፡ ሁሉ ፡ ትሩፋት
ማንንም ፡ ለዚህ ፡ አይረዳም
ሰው ፡ በሙሉ ፡ ኃይል ፡ ቢተጋም
ነፍሱን ፡ ለማዳን ፡ አይበቃም
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ በመስቀሉ
ለእኛ ፡ ፀጋን ፡ አዘጋጀ
ሞትን ፡ በመቀበሉ
ሕይወት ፡ ለነፍሣችን ፡ ዋጀ
ወደ ፡ እርሱም ፡ የሚመጣ
ይድናል ፡ ከአምላክ ፡ ቁጣ
በምሥራቺ ፡ ያመነ
በመድኃኒቱ ፡ ይድናል
ምሉዕ ፡ ተስፋ ፡ አለነ
መጽሐፍ ፡ እንዲህ ፡ ይለናል
ወልድ ፡ ያለው ፡ ሕይወት ፡ አለው
ሕይወት ፡ የለውም ፡ ወልድ ፡ ለሌለው
|