የአምላክ ፡ ቃል ፡ ያሸንፋል (YeAmlak Qal Yashenifal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የአምላክ ፡ ቃል ፡ ያሸንፋል
የጨለማውን ፡ ጭፍራ
ሰላም ፡ ላጡ
ለወደቁ
ይሰጣል ፡ ጽኑ ፡ ተስፋ

በትዕዛዙ
ሰባኮቹ
ወጡ ፡ በመላ ፡ ዓለም
ክፉ ፡ ቅናት
ሰይፍ ፡ ወይስ ፡ እሣት
ወንጌሉን ፡ አያስቀርም

ለጨካኞች
ላመጸኞች
ጽድቅን ፡ ይሰብካሉ
በጨለማ
እንዲበራ
ብርሃኑን ፡ ያቆማሉ

በዓለሙ
ይዘራሉ
አምላክ ፡ ዘሩን ፡ ያለማል
በምሕረት ፡ ቀን
አንድ ፡ ነፍስ ፡ ቢድን
አምላክን ፡ ደስ ፡ ያሰኛል

ልዑል ፡ ንጉሥ
በኛ ፡ ንገሥ
ግዛትህንም ፡ አስፋ
ድል ፡ የአንተ ፡ ነው
በዓለሙ
ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና