የአምላክ ፡ ሕዝብ ፡ የጽዮን ፡ ወገን (YeAmlak Hizb Yetsion Wogen)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የአምላክ ፡ ሕዝብ ፡ የጽዮን ፡ ወገን
ወደ ፡ ላይ ፡ ይራመዳል
በዓለም ፡ ባይገኝለት ፡ ተገን
ከአምላክ ፡ ዘንድ ፡ ተገኝቷል
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የገዛቸው
በእርሱም ፡ የሚያምኑ
እንግዶች ፡ በምድር ፡ ናቸው
በዓለምም ፡ ተበተኑ

በዓለም ፡ ሁሉ ፡ ብትጠላ
ጥሉ ፡ አያስፈራህም
ኢየሱስ ፡ ልብህን ፡ ከሞላ
ሌላ ፡ አያስፈልግም
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ምሉ ፡ ተስፋ
ሊሆንልህ ፡ ይችላል
ሌላ ፡ ምርኩዝም ፡ ቢጠፋ
ደገፋው ፡ ይጦርሃል

እርሱን ፡ አግኝተህ ፡ በምሉ
ሕይወትህ ፡ ይበቃሃል
አምላክ ፡ ሁሉ ፡ ነው ፡ በሁሉ
መንጋውንም ፡ ያስጠልላል
ድንቢጥ ፡ ቤቷን ፡ አገኘች
በአምላክ ፡ መሠዊያ
ግሩም ፡ ዓርነትም ፡ ተገኘች
ለተጨነቀው ፡ ባርያ

ዕምነትና ፡ ፍቅር ፡ ብቻ
አምላክ ፡ ከኛ ፡ ፈለገ
ፍቅር ፡ ነው ፡ የሕግ ፡ ዳርቻ
ትዕዛዙን ፡ አደረገ
የሚያምንም ፡ ይድናል
ኢየሱስ ፡ መንፈስህ ፡ ይምራን
ፍቅርህን ፡ ያስፈልገናል
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ፍቅርህ ፡ ይግዛን

መንፈስህ ፡ በዚህ ፡ መሠረት
ቅዱስ ፡ ቤትህን ፡ ይሥራ
እያንዳንዳችንንም ፡ በዕምነት
ወደ ፡ መስቀልህ ፡ ይምራ
ማኅበርህን ፡ ያዳብር
ይግለጥለት ፡ ዕውነቱን
ሁሉንም ፡ ሲያስተባብር
በሁሉ ፡ አንድ ፡ ልብ ፡ ይሁን